Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አየር መንገዱ ለ”ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት” ተጓዦች የ20 በመቶ ቅናሽ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት ጥሪ ሁለተኛ ክፍል የሆነው “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት” ጥሪን ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአየር ጉዞ ትኬት ዋጋ ላይ 20 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።

በዚሁ መሰረት ወደ ሀገር ቤት ተጓዦች ትኬታቸውን ከፈረንጆቹ ሚያዝያ 6 እስከ ሚያዝያ 21 ቀን 2022 በመቁረጥ እና ጉዟቸውን ከሚያዝያ 25 እስከ ግንቦት 15 ቀን 2022 ድረስ በማመቻቸት የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል።

ተጓዦቹ ወደ ሀገር ቤት ከመጡ በኋላም በተዘጋጁላቸው ልዩ ልዩ መርሀ ግብሮች ላይ እንዲታደሙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ጋብዟል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version