አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ምቹ የዲጂታል ስነ ምህዳርን ለመፍጠር የጀመረችውን ሥራ የሳዑዲ መንግስት እንደሚደግፍ አስታወቀ፡፡
ዓለም አቀፉ የሥራ ፈጠራ ምክር ቤት በሪያድ ባካሄደው አውደ ጥናት የተሳተፉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ሁሪያ አሊ በሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ምቹ የዲጂታል ስነ ምህዳር የመፍጠር ሥራን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በዚሁ ወቅት የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ይህንን ምቹ የዲጂታል ስነ ምህዳር ፈጠራ ሥራን እንደሚደግፍ አስታውቋል፡፡
ሚኒስትር ዲኤታዋ ግዙፉን የነዳጅ ኩባንያ አራምኮን የነዳጅ ስርጭቱን የሚቆጣጠርበትን የዲጂታል አሰራር የጎበኙ ሲሆን÷ ኩባንያው የነዳጅ ቁጥጥሩን ሙሉ ለሙሉ በዲጂታል አሰራር እየተገበረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ይህንኑ ልምድም ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት እናደርጋለን ብለዋል።
በጉባኤው ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተውጣጡ የመንግስት የቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጅ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች መሳተፋቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!