Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች ከአፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርኣያ እና ምክትል ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ ከአፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የዝግጅት ምዕራፍ አፈጻጸም ዙሪያ መክረዋል፡፡

ፕሮፈሰር መስፍን÷ኮሚሽኑ ከየካቲት 15 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ስራ መጀመሩን እና ኮሚሽኑን ከማደራጃት አኳያ አጋዥ ናቸው ካሏቸው የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር መወያየታቸውን አብራርተዋል፡፡

ኮሚሽኑ በቅርቡ የቅድመ ውይይት እቅዱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግም ዋና ኮሚሽነሩ መናገራቸውን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version