Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ አሕመድ ሽዴ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ኮርፖሬሽን የግሉን ዘርፍ ለማሳደግ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አደነቁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ የግሉን ዘርፍ ለማሳደግ እያደረገ ስላለው ድጋፍ አድናቆታቸውን ገለፁ፡፡
አቶ አሕመድ ሽዴ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ኮርፖሬሽን የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተርን ጁሞኬ ጃጉን ዶኩሙን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም የዓለም ገንዘብ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ የግሉን ዘርፍ ለማሳደግ እያደረገ ስላለው ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልጸው፥ ተቋሙ የግሉ ዘርፍ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር መሰረት ለጣሉ ፕሮጀክቶች የቴክኒክ እና የኢኮኖሚ አዋጪነት ያላቸው ጥናቶች እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የቴሌኮሙዩኒኬሽን ዘፍን ለግሉ ዘርፍ የመክፈት ሂደት ላይ ለማስፈፀም በሚያደረገው ጥረት ላይ ተቋሙ ያሳየውን ድጋፍ በሌሎች ዘርፎች አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡
የዓለም አቀፍ የገንዘብ ኮርፖሬሽን የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ጁሞኬ ጃጉን ዶኩሙ ተቋማቸው ከኢትዮጵያ ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዳለው አስታውሰው ፥ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ የግሉን ዘርፍ ኢንቨስትመንት እየደገፈ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡
አክለውም በቀጣይ በሀይል አቅርቦት፣ በጤና፣ በቤት ልማት እና በፋይናንስ ዘርፎች ቅድሚያ በመስጠት ድጋፍ እንደሚያደርጉ መናገራቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በቀጣይም የኢትዮጵያ መንግሥት የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ሚና ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እያደረገ ያለውን ጥረት እንዲሁም የባንኩን ዘርፍ ለውጭ የፋይናንስ ተቋማት የመክፈት ሂደት ላይ ተቋሙ ድጋፍ እንደሚያደረግ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version