አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በ22 ከተሞች የውሃ ብክነትን ለመቀነስ የሚያስችሉ ዘመናዊ የውሃ ፍሰት የሚለኩና የሚቆጣጠሩ መሳሪያዎችን ለማስገጠም ከሁለት ድርጅቶች ጋር ስምምነት ተፈራረመ፡፡
በሚኒስቴሩ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ እና ጂ ሲክስ ትሬዲንግን በመወከል ደግሞ የድርጅቱ ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሉጌታ በላይሁን፣ አግራባት ኮንስትራክሽንና ዋዳ ኢንጂነሪንግን በመወከል ደግሞ ወይዘሪት ፍጹም ብርሃን አማኑኤል ስምምነቱን ተፈራመዋል፡፡
በ22 ከተሞች የሚተከሉት የውሃ ቆጣሪዎችና በውሃ መስመሮች ላይ የውሃ ፍሰትን የሚለኩና የሚቆጣጠሩ ዘመናዊ መሣሪያዎች ከውሃ አቅርቦት ጋር በተያያዘ በመስመሮች ላይ በሚከሰቱ ልዩ ልዩ ችግሮች ሳቢያ የሚኖረውን ከፍተኛ የውሃ ብክነት እንደሚቀንሰው በፊርማ ስነ ስርዓቱ ወቅት ተገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ ከውሃ አቅርቦት ጋር በተያያዘ ከ35 እስከ 40 በመቶ የሚሆነው ውሃም እንደሚባክን ተጠቁሟል፡፡
ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ለማድረግ ከ482 ሚሊየን ብር በላይ በጀት የተመደበ ሲሆን÷ ገንዘቡ ከዓለም ባንክ ለሁለተኛው የከተሞች መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ፕሮግራም ከተያዘው በጀት የተገኘ ነው ተብሏል፡፡
የውሃ ቆጣሪዎቹን፣ የፍሳሽ ጠቋሚና መቆጣጠሪያ መሣሪያዎቹን ወደ ሀገር የማስገባትና ገጠማ ሥራው በአምስት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል መባሉን ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!