አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቶማስ ሳንካራ ግድያ የተከሰሱትና ለወራት ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ የቆዩት የቡርኪናፋሶ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ብሌዝ ኮምፓኦሬ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል፡፡
በፈረንጆቹ ጥቅምት 15 ቀን 1987 የተገደለውን የቶማስ ሳንካራ ግድያ ለማጣራት የስድስት ወራት የፍርድ ሂደት የወሰደው የኦጋዶጉ ፍርድ ቤት በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን የፍርድ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
በሳንካራ ግድያ ጥፋተኛ የተባሉት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ብሌዝ ኮምፓኦሬ እና ረዳቶቹ ጊልበርት ዳይንደርሬ እና ካፋንዶ ሃይሲንቴ በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ የኦጋዶጉ ፍርድ ቤት ወስኗል፡፡
የፓን አፍሪካኒዝም መሪው ቶማስ ሳንካራ ከ12 ሰዎች ጋር በደረሰበት ጥቃት በፈረንጆቹ 1987 መሞቱን የአልጀዚራ እና ሲ ጅ ቲ ኤን ዘገባዎች አስታውሰዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!