Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አገር አቀፍ የወጣቶች የከተማ ግብርና ንቅናቄ ማብሰሪያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አገር አቀፍ የወጣቶች የከተማ ግብርና ንቅናቄ ማብሰሪያ መርሃ ግብር በቦሌ ክፍለ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመርሃ ግብሩ ከሁሉም የአገሪቱ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ስራ አስፈጻሚ አባላት እንዲሁም የቦሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ተሳትፈዋል፡፡

የከተማ ግብርና ንቅናቄ መርሃ ግብሩ እየተካሄደ ያለው “ምግቤን ከጓሮዬ” በሚል መሪ ቃል ሲሆን÷ በመርሃ ግብሩ ላይ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባላት ዶክተር አለሙ ስሜ እና አቶ መለስ አለሙ መገኘታቸውን ከብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version