የሀገር ውስጥ ዜና

ተጠባቂው የሸገር ደርቢ በቅዱስ ጊዮርጊስ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

By Alemayehu Geremew

April 05, 2022

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 17ኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ቡናን ከቅዱስ ጊዮርጊስ አገናኝቷል።

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው ጨዋታ ፈረሰኞቹ ድል ቀንቷቸዋል።

ጨዋታው 4 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲጠናቀቅ፥ አቤል ያለው፣ ቸርነት ጉግሳ፣ ፍሪምፖንግ ማንሱ እና አዲስ ግደይ የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎም ቅዱስ ጊዮርጊስ 37 ነጥቦችን በመሰብሰብ መሪነቱን አጠናክሯል።

photo credit; Soccer Ethiopia