የሀገር ውስጥ ዜና

ግብርና ሚኒስቴር ለክልል ግብርና ቢሮዎች እና ለተጠሪ ተቋማት የተሽከርካሪዎች ድጋፍ አደረገ

By Meseret Awoke

April 05, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብርና ሚኒስቴር ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ያገኛቸውን 80 ተሽከርካሪዎች ለክልሎች እና ተጠሪ ተቋማት ድጋፍ አድርጓል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለአማራ፣ ኦሮሚያ ደቡብ፣ ሲዳማ እና አፋር ክልል ግብርና ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት ነው የተሽከርካሪ ድጋፍ ያበረተው፡፡

የግብርና ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን የተሽከርካሪ ድጋፉ በዋናነት የተጀመረውን የመስኖ ስንዴ ልማት አጠናክሮ ለማስቀጠል፣ በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም እና የመሬት አስተዳደር ስራዎችን ለማቀላጠፍ ታስቦ የተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም አርሶ አደሮች ከፋይናንስ ተቋማት የመበደር ዋስትና እንዲኖራቸው በማድረግ ቴክኖሎጂዎችን የመግዛት አቅም እንዲኖራቸው በማስቻል የግብርና ምርትና ምርታማነት የማሳደግ ስራን ማስቀጠል እና በሌሎችም ጥሩ አፈፃፀም ያላቸውን ዞኖችና ወረዳዎች ለማነቃቃት እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

ተሽከርካሪዎቹን በአግባቡ በመጠቀም ግብርናን ለማሻገር ለሚሰሩ ስራዎች ማዋል እንደሚገባ በማሳሰብ መሰል ድጋፎች ለሌሎች ዞኖችና ወረዳዎች ወደ ፊት እንደሚቀጥል መግለፃቸውን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!