አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚያዚያ ወር የቤንዚን እና የናፍጣ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በመጋቢት ወር ሲሸጥበት በነበረው እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ነገር ግን የአውሮፕላን ነዳጅ፣ የከባድ ጥቁር ናፍጣ እና ቀላል ጥቁር ናፍጣ የመሸጫ ዋጋ በዓለም አቀፍ ዋጋ መሰረት ተሰልቶ የመጣው ወደ ተጠቃሚው እንዲተላለፍ መወሰኑን ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡
በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግ እንደሚችልም ተጠቁሟል፡፡
የወቅታዊ የዓለም አቀፍ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ከመሆነ ጋር ተያይዞም ሸማቹ ህብረተሰብ የነዳጅ ምርቶችን በቁጠባ የመጠቀም ባህሉን በማዳበር መንግስት ለዘርፉ የሚያወጣውን ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ እንዲሁም ድጎማ ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!