አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምርት ጥራትን ለማስጠበቅ እየተሰራ መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለፀ፡፡
መንግስት የምርቶችን ጥራት ለማስጠበቅ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም የተፈለገውን ለውጥ ማምጣት እንዳልተቻለ ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ የፈረመችው የአፍሪካ አህጉራዊ የንግድ ስምምነት ተግባራዊ መሆኑ በምርት ጥራት ላይ ትኩረት ሰጥቶ የመስራትን አስፈላጊነት ይጨምራል ተብሏል፡፡
1 ነጥብ 3 ቢሊየን ህዝብ በሚሳተፍበት እና 3 ትሪሊየን የአሜሪካ ዶላር ግብይት በሚፈጸምበት የአፍሪካ የንግድ ቀጠና ለመሳተፍ መንግስት ለምርት ጥራት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡
የንግድ ስርዓቱን በማዘመን አገልግሎት መስጠት ተገቢ በመሆኑ ሚኒስቴሩ የንግድ ምዝገባና ፍቃድ ስርዓቱን ዘመናዊ በማድረግ አገልግሎቱን ኦንላይን መስጠት ጀምሯልም ነው የተባለው፡፡
የንግድ ስርዓቱን ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባም አሳስቧል፡፡
ሚኒስቴሩ ደረጃ በወጣላቸው የንግድ ዕቃዎች እና የምርቶች ጥራትና የምልክት አጠቃቀም ዙሪያ ከአምራቾች፣ ከአስመጪዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር መወያየቱን ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!