አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሳዑዲዓረቢያ ጂዳ 1 ሺህ 270 ዜጎች በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
በሳውዲ ዓረቢያ፣ በሪያድ እና የጅዳ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎቻችን የመመለስ ተግባር ቀጥሏል።
በዛሬው ዕለትም ከሳዑዲ ዓረቢያ፣ ጂዳ በተደረጉ ሶስት በረራዎች 269 ህጻናትን ጨምሮ 1270 ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።
ተመላሾች ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በሳዑዲ ዓረቢያ እስር ቤቶች እና ማዕከላት ውስጥ ያሉ ዜጎችን ወደ ሃገር ቤት ማምጣቱ በሳምንት ለሶስት ቀናት በቀን ሶስት ግዜ በሚደረግ በረራ የመመለሱ ስራ እንደሚቀጥል ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!