አዲሰ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ባለቤቷ አትሌት አልማዝ አያና ወደ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ተመልሳለች፡፡
በብራዚሉ ሪዮ ኦሊምፒክ የ 10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነችው አትሌት አልማዝ አያና ከእግር ጉዳት እንዲሁም ከወሊድ መልስ እንደገና ወደ ውድድር ተመልሳለች።
አትሌት አልማዝ ትናንትና በስፔን ማድሪድ ግማሽ ማራቶን የተወዳደረች ሲሆን 1 ሰዓት ከ8 ደቂቃ 22 ሰከንድ በመግባት 5ኛ ደረጃን ይዛ ውድድሩን አጠናቃለች፡፡
በውድድሩ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ቤተልሄም አፈንጉስ 3ኛ ደረጃን ይዛ ስታጠናቅቅ ኬኒያዊቷ ዊንፈሪዳ ውድድሩን በበላይነት አጠናቃለች፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!