የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች መካከል የተፈረመውን የሠላም ሥምምነት አደነቁ

By Mekoya Hailemariam

April 03, 2022

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች መካከል የተፈረመውን የሠላም ሥምምነት አደነቁ።

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ሀይሎች መሪዎች በወታደራዊ አቅርቦት ላይ ሳይስማሙ ያቆዩትን ጉዳይ እልባት ሰጥተው ዛሬ የሠላም ሥምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ይህንን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባወጡት መግለጫ ስምምነቱን አድንቀዋል።

ኢትዮጵያ ሁልጊዜ ከደቡብ ሱዳን ጎን እንደምትቆምም አረጋግጠዋል።

በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም እና ልማት ለማምጣት የሚደረግ ጥረትን መደገፏን እንደምትቀጥልም ነው ያስታወቁት።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!