የሀገር ውስጥ ዜና

አስተዳደሩ ‘‘ያሬድ ትምህርት ቤት ሊፈርስ ነው’’ በሚል የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም የተሳሳተ መሆኑን አስታወቀ

By Meseret Awoke

April 03, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ‘‘ያሬድ ትምህርት ቤት ሊፈርስ ነው’’ በሚል የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም የተሳሳተ መሆኑን አስታወቀ፡፡

አስተዳደሩ በማህበራዊ በትስስር ገጹ እንዳስታወቀው፥ አንዳንድ ወገኖች የተሳሳቱ መረጃዎችን በተደጋጋሚ በመልቀቅ ህብረተሰቡን ወደ ውዥንብር ለመክተት ጥረት እያደረጉ ይገኛል፡፡

በዚህ ሰሞን ‘‘አንጋፋው የሙዚቃ ትምህርት ተቋም የሆነው ያሬድ ትምህርት ቤት ሊፈርስ ነው’’ የሚል መረጃ በማሰራጨት በህዝቡ ውስጥ ውዥንብር ለመፍጠር የሞከሩ መሆኑን ያስታወቀው አስተዳደሩ ፥ ነገር ግን በአስተዳደሩም በኩል ይሁን በትምህርት ቤቱ በኩል ምንም የተለየ ነገር የሌለና ይህ መረጃ ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በዚህም ህብረተሰቡ እንደዚህ በተደጋጋሚ የሃሰት የበሬ ወለደ መረጃዎችን የሚያሰራጩ አካላትን በማጋለጥ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!