አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረ ብርሃን ከተማ በኤሌክትሪክ ሃይል የምትሰራ እና 4 ሰዎችን የመጫን አቅም ያላት ባለ 3 እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) በአንድ ስራ ፈጣሪ መሰራቷ ተገልጿል፡፡
የተሽከርካሪዋ አምራች አቶ መቅድም ኃይሉ እንደሚሉት÷ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዋ በአብዛኛው አገር ውስጥ የሚገኙ ግብዓቶችን በመገጣጠም ነው የተሰራችው፡፡
በወርክ ሾፓቸው የተሰራችው ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዋ÷ በማንኛውም የኤሌክትሪክ ቻርጀር ለ3 ሰዓታት ቻርጅ ተደርጋ በሰዓት 40 ኪሎ ሜትር መጓዝ የምትችል መሆኗን አስረድተዋል፡፡
በኤሌክትሪክ ሃይል የምተሰራው ይህች ባለሦስት እግር ተሽከርካሪ ሾፌሩን ጨምሮ 4 ሰዎችን የመጫን አቅም እንዳላትም ተናግረዋል፡፡
ተሸከርካሪዋን መጠቀም የሚቻለው ለከተማ ውስጥ የታክሲ አገልግሎት ሲሆን÷ ነገርግን ጠጠር መንገድ ውስጥም ገብታ ያለምንም ችግር መስራት እንድትችል ከነባሮቹ ባጃጆች በተለየ መልኩ ጎማዋ ከፍ ተደርጎ የተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ባለሦስት እግር ተሸከርካሪዋ በአሁኑ ሰዓት ለገበያ ብትቀርብ 160 ሺህ ብር ልትሸጥ እንደምትችል ነው አቶ መቅድም የተናገሩት፡፡
አሁን በስራ ላይ ያሉት በነዳጅ የሚሰሩት ተሸከርካሪዎች በአገልግሎት ዘመናቸው ወጪያቸው ከፍተኛ ነው ያሉት አቶ መቅድም÷እሳቸው ያመረቷት የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ግን ትልቁ ጥቅሟ በማንኛውም የኤሌክትሪክ ቻርጀር 3 ሰዓት ቻርጅ ተደርጋ በስራ ሂደት ውስጥ ያለን ከፍተኛ ወጭ በእጅጉ ትቀንሳለች ብለዋል፡፡
በቀጣይም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የፈጠራ ስራቸውን ለማስፋት እና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እቅድ እንዳላቸውም መናገራቸውን ከሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!