Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሲዳማ ክልል በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከ3.9 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከ3.9 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን ገለጸ።
ባለስልጣኑ በዘንድሮው በጀት ዓመት 5.5 ቢሊየን ብር ገቢ ለማስገባት አቅዶ እየሰራ መሆኑን የባለስልጣኑ ኃላፊ አቶ ኃይሉ ጉዱራ ተናግረዋል።
ክልሉ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ለመሰብሰብ ካቀደው ገቢ 60 ከመቶ በላይ ከተለያዩ ከገቢ ምንጮች መሰብሰቡን ነው የተገለጸው።
የተቀረው 39 በመቶ በላይ ከመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ የተሰበሰበ መሆኑን ነዉ አቶ ኃይሉ የተናገሩት።
በዘርፉ የሚታዩ ሌብነት፣ በደረሰኝ ላይ ልዩነት እንዲፈጠር ማድረግ፣ ለገቢ ተብሎ ወጪ የተደረገ ደረሰኝ አለመመለስ፣ ለስርቆት እንዲያመች ፎርጅድ ደረሰኝ መጠቀም፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማነስና አዲስ የንግድ ፍቃድ ላይ ችግሮች መኖራቸው ክልሉ ያቀደውን ገቢ በሚፈልገው ልክ እንዳይሰበስብ እንቅፋት ሆነውበታል ተብሏል።
የክልሉ መንግስት በ2013 የግብር ዘመን ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ ግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች በዛሬዉ ዕለት እውቅናና ሽልማት ሰጥቷል።
በጀማል ከዲሮና ተመስገን ቡልቡሎ
Exit mobile version