Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የላከው ሰብዓዊ ድጋፍ ትግራይ ክልል ደረሰ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የህክምና፣ ምግብ እና የውሃ ማጣሪያ ግብዓቶችን ያካተተ ድጋፍ ዛሬ ትግራይ ክልል መድረሱን አስታወቀ፡፡
የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የላከው ይህ ድጋፍ፥ እ.ኤ.አ ከመስከረም 2021 በኋላ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ክልሉ የደረሰ የመጀመሪያው የተቋሙ ሰብዓዊ ዕርዳታ መሆኑንም ከኮሚቴው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በርካታ ተሽከርካሪዎች በአፋር ክልል አብዓላ በኩል ሰብአዊ እርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ ክልል በመጓዝ ወደ ስፍራው የደረሱና በዛሬው እለትም የሚደርሱ እንዳሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መገለጹ ይታወሳል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version