በሌላ በኩል ርዕሰ መስተዳድሩ የአንገረብ የመጠጥ ውሃ ግድብን የሥራ አፈጻጸም ዛሬ ማምሻውን ተመልክተዋል፡፡
የጎንደር ከተማን የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት በማገዝ በኩል የክልሉ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ነው ዶክተር ይልቃል የተናገሩት፡፡
በከተማው በፍጥነት እየጨመረ ከመጣው የነዋሪው ህዝብ ቁጥር አንጻር የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት በበቂ መጠን ማዳረስ አልተቻለም ብለዋል፡፡
የከተማውን የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር በዘላቂነት ከመፍታት አንጻር የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ግድብ ግንባታ እንዲፋጠን ጥረት እንደሚደረግ ገልጸው፤ ሌሎች አማራጮችን ማመቻቸት ጊዜ የሚሰጠው ተግባር አለመሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ለረጅም ዓመታት አገልግሎት የሰጠውን የአንገረብ የመጠጥ ውሃ ግድብ በደለል የመሞላት ችግር በመፍታት በቴክኖሎጂ ታግዞ ውሃ የመያዝ አቅሙን ለማሳደግ የተጀመረውን ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡