Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ ቀጠናዊ የሰራተኞች ፍልሰት ጉዳይ ምክክር የሚኒስትሮች ፎረም ሊቀ-መንበርነትን ተረከበች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ቀጠናዊ የሰራተኞች ፍልሰት ጉዳይ ምክክር የሚኒስትሮች ፎረም ሊቀ-መንበርነትን መረከብዋ ተገለፀ፡፡
አስራ አንድ የምስራቅና አፍሪካ ቀንድ ሀገራት የሚሳተፉበት ቀጠናዊ የሰራተኞች ፍልሰት ጉዳይ ምክክር የሚኒስትሮች ፎረም ላለፉት ስድስት ቀናት በናይሮቢ ሲካሄድ ቆይቷል።
ላለፉት ሁለት አመታት ኬንያ የሚኒስትሮች ፎረሙን ስትመራ ቆይታለች፡፡
የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈርያት ከሚል የኬንያ መንግስት ላደረገላቸው ደማቅ አቀባበል እና ቆይታቸው የተሳካ እንዲሆን ለነበረው ዝግጅት አመስግነዋል፡፡ በተለይም ለሀገሪቱ የሰራተኞች ሚኒስትር ስሞን ቼሉጉዊ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version