Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ መምህር አማኑኤል ባልቻ የተሠሩ ድሮኖች የተሳካ በረራ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆነው አማኑኤል ባልቻ የሠራቸው ድሮኖች (ሰው አልባ አውሮፕላኖች) ያደረጉትን የሙከራ በረራ ስኬት ማጠናቀቃቸውን ዩኒቨርሲቲው ገለጸ፡፡

በአካባቢው በሚገኙ ዕቃዎች ያመረታቸውን “አውሮፕላኖች” በደምቢ ዶሎ ከተማ አውሮፕላን ማረፊያ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ሌሎች የማህበረሰቡ አባላት በተገኙበት ያደረጉትን የሙከራ በረራ በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል፡፡

በአውሮፕላን ማረፊያው የነበረው የአየር ሁኔታ ለበረራ አመቺ ባይሆንም÷ ይህንኑ የአየር ንብረት በመቋቋም ነው በመምህር አማኑኤል ባልቻ የተሠሩ አውሮፕላኖች በረራቸውን በስኬት የፈጸሙት፡፡

መምህር አማኑኤል ከዚህ ቀደም ድሮን በማምረት ለጉብኝት በማቅረብ የተሳካ በረራ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

Exit mobile version