የሀገር ውስጥ ዜና

የለገጣፎ ለገዳዲ የእግር ኳስ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን አረጋገጠ

By Alemayehu Geremew

April 01, 2022

አዲስ አበባ፣መጋቢት 23፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ተሳታፊ የነበረው የለገጣፎ ለገዳዲ የእግር ኳስ ቡድን ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል፡፡

ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው “የምድብ ለ” ጨዋታ ሰንዳፋ በኬን 4- ለ 0 ያሸነፈው ለገጣፎ ለገዳዲ የእግር ኳስ ቡድን በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ መሆኑን አረጋግጧል።

የለገጣፎ ለገዳዲን የማሸነፊያ ጎሎች ኪሩቤል ወንድሙ፣ፋሲል አስማማው፣ዳዊት ቀለመወርቅ እና ልደቱ ለማ አስቆጥረዋል፡፡

ረፋድ ላይ በተደረገ የከፍተኛ ሊግ ጨዋታ ቤንች ማጂ ቡና ኮልፌ ቀራኒዮን 2 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል፡፡