አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል ከኢትዮጵያ ለሚሄዱ ጎብኚዎች በቡድን ቪዛ ላይ ከሁለት ዓመታት በላይ ጥላው የነበረው እገዳ መነሳቱ ተገለጸ፡፡
በእየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ገዳም አባቶች፣ በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እና ከእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም ከሕዝብና ኢሚግሬሽን ጉዳይ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በተደረገ ምክክር ነው እገዳው የተነሳው፡፡
አምባሳደር ረታ ዓለሙ÷ በሂደቱ ከፍተኛ ሚና ለነበራቸው የመንግሥት አካላት እና የእስራኤል መንግስት የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት በመገንዘብ እገዳው እንዲነሳ በመፍቀዱ ምስጋና አቅርበዋል።
የእስራኤል የፓርላማ አባል አቶ ጋዲ ይባርከን እገዳው በመነሳቱ “የእስራኤል አምላክ ፈቃድ ሆኖ ይህ መልካም ዜና ለኢትዮጵያውያን በመድረሱ ደስታዬ ከፍ ያለ ነው ብለዋል።
በእየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ እንባቆም በበኩላቸው÷ “ምዕመናን ከመላው ዓለም ወደ እየሩሳሌም እየመጡ የሚያከብሩት በዓል በኮሮና ምክንያት ለሁለት ዓመታት ዝግ ሆኖ ከቆየ በኋላ በመከፈቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
እገዳው ተነስቶ የትንሳዔ በዓልን ለማክበር ወደ እስራኤል ከሚመጡ ኢትዮጵያውያን ጋር ለመገናኘት የእግዚአብሔር ፈቃድ በመሆኑ ደስታችን ታላቅ ነው ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!