የሀገር ውስጥ ዜና

በጦርነቱ የተፈናቀሉ ዜጎችን እና ከዓረብ ሀገራት ተመላሾችን ወደ ሥራ ለማስገባት በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ

By Alemayehu Geremew

April 01, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከስደት ተመላሽ ወገኖችን በማሠልጠን ወደ ሥራ ለማሰማራት ከፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም ከክልል እና ከፌደራል መንግስት አመራሮች ጋር ተወይይቷል፡፡

በሀገር አቀፍ የምክክር መድረኩ በጦርነት ሳቢያ ጉዳት የደረሰባቸውን የአንድ ማዕከል አገልግሎት መሥጫ ተቋማት፣ ኢንተርፕራይዞች እና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መልሶ ለማደራጀት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን÷ ከዓረብ ሀገራት ተገፍተው የሚመለሱ ዜጎችን ተቀብሎ ወደ ሥራ ለማሰማራት ተቀናጅቶ መሥራት እንደሚጠይቅ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በቀጣዮቹ ወራት ከ100 ሺህ በላይ ከውጭ ሀገራት ዜጎች ስለሚመለሱ መልሶ ለማቋቋም ሥልጠና በመስጠት የሥራ ዕድሎች ይመቻቻሉ ነው የሉት፡፡

ለዚህም ክልሎች፣ የፋይናንስ ተቋማት እና ባለድርሻ አካላትን ድጋፍ እንዲያደርጉ አቶ ንጉሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በጦርነቱ ምክንያት በርካታ ዜጎች ከሥራ ውጭ ሲሆኑ÷ በወደሙ የሙያ ማሰልጠኛ ማዕከላት ምክንያትም ዜጎች ከሥልጠና ውጭ መሆናቸውም ተነግሯል፡፡

የፋይናንስ ተቋማት በተለይም ባንኮች ብድር ማመቻቸት እና ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር አለባቸው መባሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡

የክልል ቢሮ ኃላፊዎች እና የሚመለከታቸው የፌደራል ተቋማት ከስደት ተመላሽ ወገኖቻችንን መረጃዎች በአግባቡ መያዝ እና ወደ ሥራ እንዲገቡ በቅንጅት መሥራት እንደሚያስፈልግም ተጠቁሟል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!