ስፓርት

ክላረንስ ሴዶርፍ ከአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ጋር አዲስ አበባ ይመጣል

By ዮሐንስ ደርበው

April 01, 2022

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የኔዘርላንድስ አማካይ ክላረንስ ሴዶርፍ ከአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ጋር አዲስ አበባ ይመጣል።

የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ሚያዚያ 2 ቀን ቅዳሜ በሸራተን አዲስ ከቀኑ 7 ሰአት ጀምሮ በሚካሄድ ስነ ስርአት በተመልካች ይጎበኛል።

ሴዶርፍም ከዋንጫው ጋር ሚያዚያ 2 ቀን ቅዳሜ በሸራተን አዲስ የሚገኝ ይሆናል።

ሴዶርፍ በተጫዋችነት ዘመኑ ከአያክስ፣ ሪያል ማድሪድ እና ኤሲ ሚላን ጋር ባለ ትልቁን ጆሮ ዋንጫ አራት ጊዜ አሸንፏል።