አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በማኅተም መሳልን የራሱ መገለጫ ያደረገው ኢትዮጵያዊ ሠዓሊና መምህር ኃይሌ ክፍሌ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴን በዚሁ የአሳሳል ዘዴ በመሣል አበርክቶላቸዋል፡፡
ሠዓሊው በታሪክ የሴቶችን ተምሳሌትነት በማሰብ በንግሥተ ሳባ፣ በእቴጌ ጣይቱ፣ በንግሥት ዘውዲቱ፣ እቴጌ መነንና ሌሎች ማኅተሞችን በመጠቀም ስሏቸዋል።
በከፍተኛ ደረጃ የሥነ ጥበብና ዲዛይን ትምህርት የተማረና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ የሥዕል ትርዒቶች ያቀረበ፣ በወርክሾፕና በሲምፖዚዬሞች የተሳተፈና በሀገርም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሥራዎቹ ሽልማት ያገኘ ሠዓሊ መሆኑንም ከፕሬዚዳንት ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!