አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ እና የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአቶ ገላሳ ዲልቦ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡
አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ÷ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ገላሳ ዲልቦ ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰባቸው እና ለወዳጆቻቸው መፅናናትን እንመኛለን ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እድሜ ልካቸውን ለህዝብ ነፃነት ሲታገሉ በኖሩት አንጋፋ የፖለቲካ ሰው በአቶ ገላሳ ዲልቦ ሕልፈተ ህይወት ከፍተኛ ሀዘን እንደተሰማቸው ገልጸዋል።
ለመላው ህዝብ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለቤተሰቦቻቸው ልባዊ መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፥ በአቶ ገላሳ ዲልቦ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸው÷ እድሜ ልካቸውን ለኦሮሞ ህዝብ የታገሉ የኦሮሞ ህዝብ ጀግና ናቸውም ብለዋል፡፡
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በበኩሉ ባወጣው መግለጫ÷ የቀድሞ የግንባሩ ሊቀመንበር በነበሩት በአቶ ገላሳ ዲልቦ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!