አዲስ አበባ፣መጋቢት 21፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ቻይና በዓለም አቀፍ ደረጃ ፈጣን የተባለውን የኤሌክትሪክ መርከብ ስራ ላይ ማዋሏን አስታውቃለች፡፡
1 ሺህ 3 መቶ መንገደኞችን የመያዝ አቅም ያለው እና በኤሌክትሪክ ባትሪዎች የሚሰራው ይህ መርከብ÷ ትናንት በመካከለኛው ቻይና ሁቤ ግዛት በይቻንግ ከተማ የመጀመሪያውን ጉዞ አድርጓል።
በቻይና የተገጣጠመው መርከቡ 100 ሜትር ርዝመት ያለው እና 7 ሺህ 500 ኪሎ ዋት አቅም ያላቸው 15 ነጠላ ባትሪዎች ያሉት ሲሆን ÷ይህም በዓለም ዘመናዊው መርከብ ያደርገዋል ነው የተባለው፡፡
የመርከቡን ግንባታ ያከናወነው ጎርጀስ ካምፓኒ ስራ አስኪያጅ ዣንግ ዩ እንደተናገሩት÷ መርከቡ በሰዓት 100 ኪሎ ሜትር የመጓዝ አቅም አለው፡፡
የመርከቡ መነሻ ወደብ ላይም የኤሌክትሪክ ሃይል መሙያ ቻርጀሮች መገጣጠማቸውን ነው የገለጹት፡፡
መርከቡ በዓመት 530 ቶን ነዳጅ በመቆጠብ በየዓመቱ ከ1ሺህ 600 ቶን በላይ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቁ በካይ ጋዞችን መቀነስ እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡
የመርከቧ የኤሌክትሪክ ሞተር ምንም አይነት ንዝረት እና ድምፅ የሌለው በመሆኑ ከሌሎች መርከቦች ጋር ሲነፃፀር ለተጓዦች የተሻለ ምቾት እንዳለውም ሲ ጂቲ ኤን ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!