Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በእስራኤል የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሃብት የሚያስተዋውቅ ዐውደ ርዕይ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በእስራኤል በተዘጋጀው ዓለምአቀፍ የቱሪዝም ጉባኤና ዐውደ ርዕይ የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሃብት የሚያስተዋውቅ ዐውደ ርዕይ ቀረበ።
በእስራኤል በየዓመቱ የሚካሄደው የቱሪዝም ጉባኤና ዐውደ ርዕይ በዚህ ዓመት “ዓለም አቀፍ የሜዲትራኒያን የቱሪዝም ገበያ 2022” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ነው፡፡
በጉባዔው መክፈቻ የእስራኤል ፕሬዚዳንት ሚር አይዛክ ሄርዞግ፣ የእስራኤል የቱሪዝም ሚኒስትር፣ ከተለያዩ አገራት የመጡ የመንግስታት ተወካዮች እና በዘርፉ የተሰማሩ አካላትና ባለሙያዎች መሳተፋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህ ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ዐውደ ርዕይ ላይ በርካታ ሀገራት በቱሪዝም ያላቸውን መስህብ ለተሳታፊዎች በምስል አቅርበዋል፡፡
በዐውደ ርዕዩ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመሆን፣ ኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት መሆኗን፣ ኢትዮጵያ ባህላዊ ቅርሶችን፣ የታሪክ ሃብት እና የማራኪ ብዝሃነቷ ነጸብራቅ የሆኑ የዓለም ድንቅ ስፍራዎችን እና የማይዳሰሱ ቅርሶችን በምስልና በገለጻ ቀርቧል።
በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ መንግስት ለመስኩ የሰጠውን ትኩረት በሚመለከት ገለጻ በማቅረብ፣ በአውደ ርዕይ ለሚሳተፉ ኢትዮጵያን፣ መጎብኘት ለሚፈልጉ እስራኤላውያን እንዲሁም አስጎብኚዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ በመግለጽ ÷ኢትዮጵያን እንዲጎበኙም ጥሪ አቅርቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version