የሀገር ውስጥ ዜና

ከወጪ ንግድ ከ7 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ አስታወቀ

By Alemayehu Geremew

March 30, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ውጭ ከላካቸው ምርቶች ከ7 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ገለጸ፡፡

ከሐምሌ ወር 2013 ዓ.ም ጀምሮ 7 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር የሚያስገኙ ምርቶችን ወደ ውጭ ለመላክ አቅዶ ከ7 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማስገኘቱን የፓርኩ ሥራ አስኪያጅ አቶ አህመድ ሠይድ ተናግረዋል።

በአሸባሪው ቡድን ከፍተኛ ውድመት የደረሰበት የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ሥራ ከተመለሰ በኋላ በሠጠው አገልግሎት ከ3 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚያወጡ ምርቶችን ወደ ውጭ ልኳል ተብሏል።

ወደ ውጭ የተላኩት ዋና ዋና ምርቶችም የወንድ ሙሉ ልብስ፣ የሴቶች ቦርሳና የስፖርት አልባሳት መሆናቸውን ያነሱት ስራ አስኪያጁ÷ በአሁኑ ሰዓት ፓርኩ ለ2 ሺህ 72 ወጣቶች የስራ እድል መፈጠሩን ገልፀዋል።

በአንድነት ናሁሰናይ