Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኮሚሽነር ለሊሴ እና አቶ አዲሱ የኪንግደምና ሰንሻይን አምራች ፋብሪካዎችን እና የኢስት ኢንዱስትሪ ዞንን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ እናበኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተሞች ልማት ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚገኙ የኪንግደም እና ሰንሻይን አምራች ፋብሪካዎችን እና የኢስት ኢንደስትሪ ዞንን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም በፓርኮቹ ውስጥ እየሰሩ ካሉ ባለሀብቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱም ባለሃብቶቹ በስራ ሂደት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ሃላፊዎቹ አስረድተዋል፡፡
ከሃላፊዎቹ የተነሱትን እክሎች ለመፍታት የሚያስችሉ የመፍትሄ አቅጣጫዎች መቀመጣቸውንም ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version