Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አንጋፋው አጥቂ ሳላዲን ሰኢድ ሲዳማ ቡናን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አንጋፋው አጥቂ ሳላዲን ሰኢድ ሲዳማ ቡናን በይፋ መቀላቀሉን ክለቡ አስታውቋል፡፡
 
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ በጉልህ ከሚነሱ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ሰላዲን ሰኢድ ሲዳማ ቡናን በይፋ መቀላቀሉ ተረጋግጧል፡፡
 
ከሙገር ስሚንቶ በኋላ ረጅም ዓመታትን በቅዱስ ጊዮርጊስ ያሳለፈው ሳላዲን ÷በግብፅ እና በቤልጅዬም ክለቦች እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ምርጥ ጊዜያትን አሳልፏል፡፡
 
ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በይፋ ከተለያየ በኋላ ክለብ አልባ የነበረው ተጫዋቹ ÷ የአሰልጣኝ ገብረመድን ሃይሌ ቡድን ለማገልገል ፊርማውን ማስቀመጡ ታውቋል፡፡
 
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማራኪ እንቅስቃሴ ማሳየት የጀመረው ሲዳማ ቡና አጠቂውን ሳላዲን ሰኢድ ማስፈረሙ የአጥቂ ክፍሉን የበለጠ ያጠናክርለታል መባሉን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version