አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የምሥራቅ አፍሪካን ማኅበረሰብ ለመቀላቀል ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱ ተገለጸ፡፡
ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የቀጠናው ሀገራት ዜጎች ያለገደብ በመንቀሳቀስ በሚያከናውኗቸው ነፃ የግብይት እና የንግድ ትሥሥር ተጠቃሚ ትሆናለች ተብሏል፡፡
የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረ-ሰብ ሊቀ መንበር እና የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በመሩት የበይነ-መረብ ጉባዔ ላይ ÷ “የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወደ ቀጠናዊ ማኅበረሰቡ መቀላቀል በቀጠናዊ ውህደቱ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ክስተት ነው” ማለታቸውን የዘገበው ሲ ጂ ቲ ኤን ነው።