አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ በኢትዮጵያ የያደረጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ አገራቸው ተመለሱ።
የጅቡቲው ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ የገቡት ባለፈው እሁድ ነበር።
በጉብኝታቸው ወቅትም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።
ምክክሩን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ሀሳብ፥ “በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ትሥሥር ታሪካዊ እና ጥልቅ መሠረት ያለው ነው” ሲሉ ገልጸውታል።
የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊና የቅርብ ግንኙነት አስመልክተውም “ከጉርብትና ያለፈ ቤተሰባዊነት ነው። ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ እና እኔ ነባሩን መሠረት ለሀገሮቻችን የጋራ ብልጽግና መሸጋገሪያ ልናደርገው ቁርጠኞች ነን” ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።
በተጨማሪም ፕሬዚዳንቱ በትናንትናው ዕለት የኢትዮጵያ የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና መስሪያ ቤትን ጎብኝተዋል።
ከጉብኝቱ በኋላ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
በውይይታቸው ወቅትም የንግድ፣ የግብርና መዋዕለ ንዋይ ፍሰት፣ የጋራ መሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ ቱሪዝም፣ ኢነርጂ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ባማከለ መልኩ ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ ውይይት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝታቸውን ያጠናቀቁትን ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌን ዛሬ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አሸኛኘት አድረገውላቸዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!