Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢ/ር ታከለ ኡማ ከወራት በፊት በ10 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በጀት የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከወራት በፊት በ10 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

በዚህም የአድዋ ማዕከል ፕሮጀክትን፣ 1 ሺህ መኪኖችን የማስቆም አቅም ያለውን የታላቁ ቤተ መንግስት የመኪና ማቆሚያ እንዲሁም በአንድ ጊዜ ከ10 ሺህ ሰው በላይ ማስተናገድ የሚችለውን የቤተ- መፅሐፍት ግንባታን ተመልክተዋል።

ከ3 እና 4 ወራት በፊት የተጀመሩት ፕሮጀክቶች ስራቸው በፍጥነት እየተከናወነ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

በከተማዋ የአድዋ ድል ማስታወሻ ከሆነው ፕሮጀክት በተጨማሪ የተለያዩ ዘመናዊ የመንገድ ግንባታዎች እየተገነቡ ይገኛሉ።

የግንባታዎቹ አፈጻጸምም አሁን ላይ 20 በመቶ የደረሰ ሲሆን ፕሮጀክቶቹ ይጠናቀቃሉ ከተባሉበት ጊዜ ቀድመው እንዲጠናቀቁ እየተሰራ ይገኛል ተብሏል።

ፕሮጀክቶቹ የከተማዋን እሴቶች የመጠበቅና የመጠቀም እንዲሁም የከተማዋን ገጽታ መቀየር ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version