አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በመንግስታቱ ድርጅት የኢፌዴሪ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ዳያስፖራው በአገር ላይ የሚሰነዘር የውጭም ሆነ የውስጥ ጫናን በአንድነት ቆሞ እንዲመክት ጠይቀዋል።
አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴና አምባሳደር ፍጹም አረጋ በመላው አሜሪካ ከሚገኙ የኮሚዩኒቲ አደረጃጀት ኃላፊዎች፣ የግብረ ኃይል እና ከሲቪል ማህበራት አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በበይነ መረብ ተወያይተዋል።
በዚሁ ወቅት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ÷ ዳያስፖራው በአገር ላይ የሚሰነዘር የውጭም ሆነ የውስጥ ጫና በአንድነት ቆሞ እንዲመክት ጠይቀዋል።
አምባሳደር ፍጹም በበኩላቸው÷ በአሜሪካ ኮንግረስ እና ሴኔት ኤች አር 6600 እና ኤስ 3199 የተሰኙ በኢትዮጵያ ላይ ለማሳለፍ የቀረቡ ረቂቅ ህጎች የአገርን ሉዓላዊነት የሚጋፉ፣ የሁለቱን አገራት ግንኙነት በእጅጉ የሚያሻክር እና ዳያስፖራውንም ከአገሩ ጋር ያለውን ትስስር የሚበጣጥስ አደገኛ እርምጃ ነው ብለዋል።
መንግስት ለአገር አንድነትና ሰላም ሲል በርካታ እርምጃዎችን እየወሰደ ባለበት ወቅት የእጅ አዙር ጫና ለማድረግ መሰል አካሄዶችን ይዞ መምጣት ገንቢ አለመሆኑን ገለጸው÷ ይህም ፈጽሞ ተቀባይነት እንደሌለው አስረድተዋል፡፡
በአሜሪካ የሚገኘው ዳያስፖራ እያደረገ የቆየውን ታሪክ የማይዘነጋው የአገር ዘብነት እነዚህ ረቂቆች እንዳይጸድቁ በማድረግም አሻራውን እንዲያሳርፍ ጥሪ አቅርበዋል።
ተሳታፊዎች በበኩላቸው በአገር እንደማይኮረፍ÷ ከመንግስት እርምጃዎች ጋር በተገናኘ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች በአገር ቀጣይነት ላይ የተደቀኑትን ረቂቅ ህጎች እንዳይጸድቁ ከመታገል አንደማያቆማቸው ገልጸዋል።
በየአካባቢያቸው የሚገኙ ተመራጮችን በስልክ፣ በኢሜል፣ ፒቲሽን በመፈረም እና በአካል በማግኘት ትክክለኛ መረጃ እንዲኖራቸው በማድረግ ለመጽደቅ በሂደት ላይ የሚገኙት ረቂቆች እንዲመክኑ የጀመሩት ስራ እንደሚያጠናክሩ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!