Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሩሲያ ምርቶቿን በሀገር ውስጥ ምንዛሬ የመሸጥ ውሳኔ በህንድ ተቀባይነት አገኘ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በምዕራባዊያን የተጣለባትን ማዕቀብ ተከትሎ ወደ ወጭ ሀገር የምትልካቸውን ምርቶቿን በሀገር ውስጥ ምንዛሬ መሸጥ እንደምትጀምር ያስተላለፈችው ውሳኔ በህንድ ተቀባይነት አግኝቷል።

በህንድ እና በሩሲያ ለሚደረገው የንግድ ልውውጥ በሩፒ እና በሩብል ክፍያ ለመፈጸም የሚያስችል ስርዓት በዚህ ሳምንት ሊጀመር እንደሚችል የህንድ ኤክስፖርት ድርጅቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኤ ሳክቲቬል ለሲኤንቢሲተናግረዋል።

ይህ የቀጥታ ግብይት ከተጀመረ ህንድ እና ሩሲያ የፋይናንስ ስራዎችን ያለዶላር እንዲያከናውኑ ያስችላቸዋል ነው የተባለው።

እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለጻ፣ የሕንድ መንግሥት ወደ 5 ለሚደርሱ የሕንድ ባንኮች የንግድ አሠራሩን በሚመለከት ፕሮፖዛል በማዘጋጀት በማዕከላዊ ባንክ ገዥ፣ በፋይናንስ ሚኒስትሩና በባንኮች መካከል በጉዳዩ ላይ ውይይት ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አርቲ ዘግቧል።
ሩስያ በምዕራባዊያን በተጣለባት ማእቀብ የተነሳ የአሜሪካን ዶላር እና ዩሮን እንደማትጠቀም ማሳወቋ ይታወሳል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version