Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጃፓን በአማራና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች በችግር ላይ የሚገኙ ወገኖችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክትይፋ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፓን መንግስት በአማራና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች በችግር ላይ የሚገኙ ወገኖችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ለአንድ አመት የሚቆይ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።

ፕሮጀክቱ በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉና ፆታዊ ጥቃት የተፈፀመባቸውን ሴቶች የሚደግፍና በስነ- ተዋልዶ ጤና ላይ አተኩሮ የሚሰራ መሆኑ ታውቋል።

ለዚህ ፕሮጀክት ስኬትም የጃፓን መንግስት 1 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን የመንግስታቱ ደርጅት የስነ-ህዝብና ፈንድ በኢትዮጵያ የፕሮጀክቱን አፈፃፀም ይከታተላል የቴክኒክ ድጋፍም ያደርጋል ተብሏል።

በፕሮጀቱ በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉና ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች እንዲሁም በኮሮና-ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ለችግር የተዳረጉትን የሚታገዙ መሆኑም ተገልጿል።

በመሆኑም ፕሮጀክቱ በአማራ ክልል በአራት ወረዳዎች (በሰሜን ሸዋ፣ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን፣ በአዊና ምዕራብ ጎጃም) ዞኖች የሚተገበር መሆኑ ተመላክቷል።

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ደግሞ በመተከል ዞን ስር ባሉ ሁለት ወረዳዎች (ዳባጤ እና ዳንጉር) ወረዳዎች የሚተገበር ይሆናል።

በመሆኑም ለእነዚህ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የጃፓን መንግስት 1 ሚሊየን ዶላር መመደቡን በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ገልጸዋል።

በተመድ የስነ-ህዝብና ፈንድ የኢትዮጵያ ተወካይ ሚስ ኢስፔራንስ ፉንዲራ÷ ፕሮጀክቱ በተለይም ሴቶች፣ ህጻናትና ሌሎችንም በችግር ላይ ያሉ ከ80 ሺህ በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።

ፕሮጀክቱ በጦርነት ሳቢያ የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለመገንባት መንግስት የሚያደርገውን ጥረት የሚደግፍ ይሆናልም ነው ያሉት።

በፕሮጀክቱ ይፋ ማድረጊያ መርሃ ግብር ላይ ከሁለቱ ክልሎች የተወከሉ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተው ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ሲደረግ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚኖረው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በጤና ሚኒስቴር የእናቶችና ህጻናት ጤና አማካሪ እዮብ ጌታቸው÷ ለፕሮጀክቱ ስኬታማነት በትብብር ለመስራት ዝግጁ ነን ሲሉ አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version