Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ የሚከለክለውን ደንብ አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ውይይት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ እና ተከራዮችን ማስወጣትን የሚከለክለው ደንብ መርምሮ አፅድቋል።
ምክር ቤቱ ደንቡን ያፀደቀው በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተስተዋለ ያለውን የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠርና በዜጎች ላይ የሚያሳድረውን ተፅእኖ ለመቀነስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው ተብሏል፡፡
አዋጁ ለሦስት ወራት እንደሚቆይና የንግድ ቦታ ኪራይን እንደማያካትት ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ÷ አዋጁ በተለይም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለው የማህበረሰብ ክፍል በኑሮ ውድነት ምክንያት እየደረሰበት የሚገኘውን ጫና ለመቀነስ እንደሚያግዝ ገልጸው÷ ለደንቡ ተፈፃሚነት የሚመለከተው ሁሉ የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ በበኩላቸው÷ በክልሉ በተለይ በአሁኑ ወቅት የቤት ኪራይ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መሆኑን አስታውሰው÷ የአዋጁ ተግባራዊ መሆን ችግሩን ለመቅረፍ ያግዛል ብለዋል፡፡

የመስተዳድር ምክር ቤቱ አባላት በሰጡት አስተያየት ለአዋጁ ተፈፃሚነት ሁሉም የበኩሉን መወጣት እና በቅንጅት መንቀሳቀስ ያስፈልጋል ብለዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version