አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጂቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑማር ጌሌ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ዋና መስሪያ ቤት ጎበኙ።
ፕሬዚዳንቱ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ትናንት አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፥ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በመሆን ዛሬ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህነንት ኤጀንሲ ዋና መስሪያ ቤት ጎብኝተዋል።
የሁለቱ አገራት መሪዎች በሁለትዮሽ አገራዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።