አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በአዲስ መልክ የተደራጀ አገር አቀፍ የህጻናት ፓርላማ ተመሰረተ።
ፓርላማው ከዚህ በፊት ሞዴል የህጻናት ፓርላማ በሚል ተቋቁሞ የነበረ ሲሆን÷ ዛሬ ጠንካራ አደረጃጀት ፈጥሮ በአዲስ መልክ ተቋቁሟል ተብሏል።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደው የምስረታ ሂደት ከሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ አባላት ተሳትፈዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንዲሁም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎችም ተገኝተዋል።
የህጻናት ፓርላማው በተለይም የህጻናት መብቶችና ደህንነትን ለማስጠበቅ የሚሰራ ይሆናል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።
ከህጻናት መብቶች ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ያጸደቀቻቸውን ህጎችና ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች በማስገንዘብ ረገድም የሕጻናት ፓርላማው ጉልህ ሚና ይኖረዋል ነው የተባለው።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!