አዲስ አበባ፣መጋቢት 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ የእሁድ ገበያ ተጠናክሮ መቀጠሉን የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡
ከተጀመረ ወራትን ያስቆጠረው የእሁድ ገበያ አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት በከተማዋ የኑሮ ውድነትን ለማቃለልና የግብይት ስርዓቱን ጤናማ ለማድረግ እንደሚያግዝ ከንቲባዋ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
የግብርና ምርቶች በተለይም አትክልት፣ ጥራጥሬ፥ የመኸር ሰብል እና የፋብሪካ ምርቶች በተሻለ አቅርቦትና በተመጣጣኝ የገበያ ዋጋ ለሸማቾች እየቀረበ እንደሚገኝም ገልፀው ነበር።
በዛሬው ዕለትም የአዲስ አበባ የእሁድ ገበያ ተጠናክሮ መቀጠሉን ነው ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ያሰፈሩት፡፡
የከተማው አስተዳደሩ በቀጣይም አምራቹ እና ሸማቹ በቀጥታ የሚገበያዩበትን ጤናማ የንግድ ስርዓት ለመፍጠር የጀመርናቸውን መሰል ተግባራት አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናልም ብለዋል ከንቲባዋ።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!