Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያዊው ፍቅሬ በቀለ በወንዶች የሮም ማራቶን አዲስ ክብረ ወሰን በማስመዝገብ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሮም የወንዶች ማራቶን ኢትዮጵያዊው ፍቅሬ በቀለ አዲስ ክብረ ወስን በማስመዝገብ አሸነፈ፡፡

አትሌቱ 2 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ48 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት አዲስ ክብረ ወሰን የሰበረ ሲሆን፥ ኬንያዊው ቤንጃሚን ኪፕቶ በ2009 ያስመዘገበውን ሪከርድ በመሰበር ነው ውድድሩን በበላይነት ያጠናቀቀው።

አትሌት ታደሰ ማሞ ውድድሩን በሁለተኝነት ሲያጠናቅቅ አትሌት አብርሃም ግርማ ደግሞ አራተኛ ሆኖ ጨርሷል።

በሴቶች በኩል አትሌት ሲጫሌ ዳላሳ በ2 ሰዓት ከ26 ደቂቃ ከ08 ሴኮንድ በመግባት ለሀገሯ ወርቅ አስገኝታለች።

በውድድሩ የተሳተፉት አትሌት ታደለች በቀለ እና የሺመቤት ታደሰ ሦስተኛ እና አራተኛ በመግባት ውድድሩን አጠናቀዋል።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

Exit mobile version