አዲስ አበባ፣መጋቢት 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን በድጋሚ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡን ገለጸ፡፡
ፓርቲው 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡
ፓርቲው በዚሁ ጉባዔው ከፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በተጨማሪ፥ አቶ በቀለ ገርባን የኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡
እንዲሁም አቶ ጁሐር መሀመድን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም ፓርቲው እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባኤው አቶ ጁሐር መሀመድን ጨምሮ 17 የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መርጧል፡፡
በጉባዔው ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፥ ህብረ ብሄራዊ ወይም ፌዴራሊዝም ማለት ሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች በሁሉም ዘርፍ ተሳታፊ የሚሆኑበት ስርዓት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አክለውም ለሰላምና እና ለሀቀኛ ዲሞክራሲ ለሚደረገው ትግል፣ ሀገሪቱን ለመለወጥ እና ብልፅግናዋን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ትግል ፓርቲያችን የራሱን አስተዋፅኦ ያርጋል ብለዋል።
ለሁለት ቀናት እየተካሄደ ባለው የፓርቲው መደበኛ ጉባኤው ከተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የተውጣጡ የፓርቲው አባላትና አመራሮች ተሳታፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ጉባኤው የተለያዩ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተጠቁሟል፡፡
በሲፈን መገርሳ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!