አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ በአፋር ክልል በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች እና በጦርነቱ የወደሙ ፖሊስ ጣቢያዎችን ለማቋቋም የሚውል ከ 4 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡
በዚህም በጥሬ ገንዘብ 400 ሺህ ብር ፣ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የፅዳት እቃዎች ፤ ከ787 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ ልዩ ልዩ የታሸጉ ምግቦች ፣ ከ1 ሚሊየን 830 ሺህ ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ለቢሮ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ኮምፒውተሮች ፣ ፎቶ ኮፒ ማሽኖች ፣ ሼልፍ ፣ ወንበሮች እና ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል፡፡