Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በድርቅ ለተጎዱ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚደረገው ድጋፍ እስከ ሚያዝያ መጨረሻ ይቀጥላል – አቶ ሙስጠፌ መሐመድ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በድርቅ ለተጎዱ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚደረገው ድጋፍ እስከ ሚያዝያ መጨረሻ ድረስ እንደሚቀጥል የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ገለጹ፡፡

አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ÷ በአቶ አብዲጀባር ሰኢድ የተመራውን ከሳዑዲ አረቢያ፣ ከተባበሩት አረብ ኢምሬቶችና ከሕንድ የተወጣጡ የሶማሌ ክልል ተወላጅ ባለሐብቶች ልዑካን ቡድን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይቱ ወቅት ባለሐብቶቹ ከቀናት በፊት የክልሉ መንግሥት በድርቅ የተጎዱትን የክልሉ ማኅበረሰብ ለመታደግ እየተደረገ ያለውን ርብርብ በመደገፍ የበኩላቸውን መወጣታቸውን ገልጸዋል።

በዚህም የባለሐብቶቹን ልዑካን ቡድን የመሩት አቶ አብዲጀባር ሰኢድ ፥ “የሶማሌ ወንድም እህቶቻችን በመርዳታችን በጣም ደስተኞች ነን” ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ፥ ባለሐብቶቹ ለህዝቡ ላደረጉላቸው ድጋፍ አመስግነው ፥ ኅብረተሰቡ ከደረሰበት የድርቅ ጉዳት እስኪያገግም መንግስት እያደረገ ያለውን ሰብዓዊ እርዳታ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ርዕሰ መስተዳድሩና ባለሐብቶቹ የሶማሌ ክልል አርብቶ አደርና ከፊል አርሶአደሩን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሠፊ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን በክልሉ ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልባቸው ዙሪያ ተወያይተውበት መግባባት ላይ መድረሳቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version