Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ምዕራባውያኑ ለሩሲያ – ዩክሬን ጦርነት መፍትሄ እንዲያፈላልጉ ባይደን ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ምዕራባውያን አጋሮቻቸው ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ለምታደርገው ጦርነት መፍትሄ እንዲያፈላልጉ ጠየቁ፡፡

ጆ ባይደን ዛሬ ወደ አውሮፓ ሃገራት አምርተዋል።

የጉዟቸው አላማም አሜሪካ ከምዕራባውያን አጋሮቿ ጎን በመቆም ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ለምታደርገው ጦርነት መፍትሄ በማፈላለጉ ረገድ ማንኛውንም ድጋፍ እንደምታደርግ ለማረጋገጥ ነው መባሉን ኤን ቢ ሲ ኒውስ ዘግቧል፡፡

ጆ ባይደን በጉዳዩ ላይ የመከሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸውን አንቶኒ ብሊንከን አካተው እንደሆነ የተመለከተ ሲሆን ፣ በተጨማሪም የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን ፣ የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሚትሮ ኩሌባ እና የዩክሬን መከላከያ ሚኒስትር ኦሌክሲይ ሬዝኒኮቭ ተካተዋል፡፡

ባይደን በውይይቱ የተሳተፉት እግረመንገዳቸውን ሲሆን ፖላንድ በሚገኘው ሜሪየት ሆቴል እንደተሰበሰቡና እንደመከሩ ነው የተገለጸው፡፡

ባይደን ጊዜያዊ መጠለያ የሚፈልጉትን በጦርነቱ ከዩክሬን ወደ ፖላንድ የገቡ ከ300 ሺህ በላይ ስደተኞች እንደሚያገኙም ነው የተነገረው፡፡

የስደተኞች ፍሰት አሁንም እንዳላቋረጠ እና ወደ ከተማዋ ባቡር ጣቢያ በየቀኑ እየገቡ እንደሆነ ነው የተመለከተው፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version