Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በህልውና ዘመቻው የላቀ የስራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የልዩ ዘመቻዎች ሃይል እና የሪፐብሊኩ የጥበቃ ሃይል አመራሮች እና አባላት የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህልው እና የህግ ማስከበር ዘመቻ እንዲሁም በዘመቻ ለህብረ ብሔራዊ አንድነት በተካሄደው ሀገር የማዳን ዘመቻ የላቀ የስራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የልዩ ዘመቻዎች ሃይል እና የሪፐብሊኩ የጥበቃ ሃይል አመራሮች እና አባላት የሜዳልያ እና እውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡
 
በመርሃ ግብሩ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።
 
የሜዳልያ እና የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብሩ በተለያዩ ወታደራዊ ትርኢቶች መጀመሩን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Exit mobile version