የሀገር ውስጥ ዜና

ከተማ አስተዳደሩ ከህብረተሰቡ የተለያዩ ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን የሚቀበልበት የስልክ ቁጥሮችን ይፋ አደረገ

By Meseret Awoke

March 25, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከህብረተሰቡ የተለያዩ ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን የሚቀበልበት የስልክ ቁጥሮችን ይፋ አድርጓል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይቶችን ሲያካሂድ የቆየ ሲሆን ፥ በውይይቶቹም ከህብረተሰቡ በርካታ ጠቃሚ ሃሳቦችንና ግብአቶችን ማሰባሰብ መቻሉ ተገልጿል፡፡

አሁንም ህብረተሰቡን ለማዳመጥ ተጨማሪ አማራጮችን መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ ማንኛውም ሰው ካለበት ሆኖ ጥቆማዎችን መስጠት የሚችልበት የስልክ ቁጥሮችን አስተዳደሩ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት ህብረተሰቡ ማንኛውንም ቅሬታና ጥቆማዎችን በነፃነት የሚሰጥባቸው የጥቆማ መስጫ የስልክ ቁጥሮችን ይፋ አድርጓል፡፡

በአጭር ቁጥር – 9977 ፤ በሞባይል ስልኮች 09 00640830 ፣ 09 00640789 ሲሆኑ ፥ አስፈላጊ የሰነድ መረጃዎችን በቴሌግራም ለማያያዝ እና ለአጭር መልእክቶች የሞባይል ቁጥሮችን መጠቀም እንደሚቻል ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!