Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ።
ምክር ቤቱ ባካሄደው መደበኛ ጉባዔው፥ በተለያዩ ክልለዊና አገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በስፋት የመከረ ሲሆን፥ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ማምሻውን ተጠናቅቋል።
በዚህም መሰረት አቶ ደሳለኝ ጣሰው የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም ዶክተር አማረ ብርሃኑ ደግሞ የክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር ሆነው ተሹመዋል፡
ምክር ቤቱ በተጨማሪም በርዕሰ መስተዳድሩ የቀረቡለትን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) የሥራ አመራር ቦርድ አባላትን ሹመት ያፀደቀ ሲሆ፥ አቶ ሙሉቀን ሰጥዬም የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሹመዋል፡፡
በተመሳሳይ የክልሉ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በርዕሰ መስተዳድሩ የቀረቡ 160 ዕጩ የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡
ጉባዔው በመጨረሻም የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችን፣ የቋሚ ኮሚቴ አባላትንና የክልሉን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሹመት በማጽደቅ ተጠናቋል።
ከተሾሙት ዳኞች ውስጥ 62ቱ (38 ነጥብ 75 በመቶ) ሴቶች ሲሆኑ፥ በዳኝነት ከተሾሙት መካከል 9 ያህሉ አካል ጉዳተኞች መሆናቸውም ታውቋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
23,105
People reached
823
Engagements
Boost post
290
15 Comments
11 Shares
Like
Comment
Share


በለይኩን ዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version